የዩክሬን የወጪ ዕህል ንግድ ሥምምነት መታደሱ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ዩክሬን በጥቁር ባሕር በኩል ዕህል እንድትነግድ የሚያስችለው ሥምምነት መታደሱን የሩሲያውን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ግሩሽኮ ተናገሩ፡፡
የወጪ ዕህል ንግድ ስምምነቱ ለቀጣይ ሦስት ወራት መታደሱንም ነው የገለጹት፡፡
አሌክሳንደር ግሩሽኮ እንዳሉት ሩሲያ የዕህል ንግድ ሥምምነቱ ለሁለት ወራት ብቻ እንዲታደስ ተስማምታለች።
ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ በተመድ እና ቱርክ አደራዳሪነት ዩክሬን የጥራጥሬ ምርቶቿን በጥቁር ባሕር በኩል ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ ሥምምነት መደረሱ ይታወሳል።
ዩክሬን ምርቷን ለገበያ እንድታቀርብ ከማድረግ ባለፈ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ማንሳትም የሥምምነቱ አካል ነው።
ይሁን እንጅ ሞስኮ ይህ ተግባራዊ አልተደረገም በሚል አሁን ወቀሳዋን እያቀረበች ነው።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይህ ጉዳይ በፍጥነት እልባት ሊሰጠው ይገባል ማለታቸውን የዘገበው አር ቲ ነው።\