የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ምዕራብ ክልል ለዞን አስተዳደሮች የተሽከርካሪ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

March 14, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ለዞን አስተዳደሮች የተሽከርካሪ ድጋፍ አደረገ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ለሥድስቱም ዞን አመራሮች እና ለቦንጋ ዳቦና ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ የተሽከርካሪዎቹን ቁልፍ አስረክብዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቅልፍ ርክክቡ ወቅት÷ ተሽከርካሪዎቹ ለመንግስታዊ ሥራ ብቻ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ አሳስበዋል።

ለሁሉም ዞኖች አንድ አንድ ተሽከርካሪ ድጋፍ መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለተመረቀው የቦንጋ ዳቦና ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካም አንድ ተሽከርካሪ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!