Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ84 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ዳዬ ከተማ ከ84 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የመሠረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት የዳዬ ነዋሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ የንፁሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት መሆኑን ጠቅሰው ÷ ሌሎች ጥያቄዎችንም ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴዔታው በበኩላቸው ÷ የዳዬ የንፁሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ይሰራል ነው ያሉት።

የንፁሕ  መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ  የዳዬ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄን የሚፈታ ፕሮጀክት ነው መባሉንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዳዬ የንፁሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ376 ሚሊየን 432 ሺህ 217 ብር እንደሚገነባና ከ84 ሺህ በላይ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናልም ተብሏል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.