Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል እና ዋዛ ፌስቲቫል መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛው ክልል አቀፍ የባህል እና ዋዛ ፌስቲቫል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀመረ።

“ባህላችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ-ቃል መከበር የጀመረው ፌስቲቫሉ ፥ በባህላዊ ሁነቶች፣ በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቪሽንና ባዛር በድምቀት መከበር ጀምሯል።

ፌስቲቫሉ በዛሬው ዕለት በፓናል ውይይት መከበር የጀመረ ሲሆን ፥ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአሶሳ ከተማ ባህላዊ እሴቶችን የሚያስተዋውቅ ኤግዚቪሽን የተከፈተ ሲሆን ፥ ኤግዚቪሽኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሣ ከፍተዋል።

ኤግዚቢሽኑ እየተከበረ የሚገኘው ክልል አቀፍ የባህል እና ዋዛ ፌስቲቫል አንዱ አካል ነውም ተብሏል።

በኤግዚቪሽኑ ላይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ አልባሣት፣ ጫማዎች፣ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች፣ የባህል መድኃኒቶች፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ጨምሮ ሌሎችም ለዕይታ ቀርበዋል።

በተጨማሪም ዋዛ የትንፋሽ መሣሪያን ጨምሮ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ጭፈራዎች ለእይታ ቀርበዋል።

በመድረኩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሠር አበባው አያሌውን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.