Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስት(ኢጋድ) ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በማህበራዊ ትስስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር በድጋሚ በመገናኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።

ኢጋድ የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና በተመለከተ እንዲሁም የኢጋድ እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በተመለከተ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር ምክክር ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል።

ሊቀመንበሩ በባለፈው አመት በኬንያ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተገኛኝተው መወያየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.