የሀገር ውስጥ ዜና

በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የሚገኙ ድርጅቶች በቀን 10 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን እያመረቱ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

April 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የሚገኙ ድርጅቶች በቀን 10 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን እያመረቱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዲስትሪዎች ወቅታዊውን ሁኔታ ከግሞት አስገብተው እየሠሩ ነው ብለዋል።

በዚህም በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የሚገኙ ድርጅቶች ሥራቸውን ሳያስታጉሉ አስቸኳይ ፍላጎቶችን ለማሟላት እየተጉ መሆኑንም ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም በቀን 10 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን እያመረቱ ሲሆን፥ የምርቱን መጠን በቀን ወደ 50 ሺህ ለማድረስ ማቀዳቸውንም ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪዎቹን ስራ ያበረታቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ “ሌሎች ድርጅቶችም ፈጠራ በታከለበት እና ለወቅቱ በሚያመች ሁኔታ ሥራቸውን እንዲከውኑ አበረታታለሁ” ብለዋል።

Our industries are adapting to the times. Companies in Hawasa Industrial Park undeterred and shifting operations to meet immediate needs. Currently producing 10k face masks per day to increase to 50k/day. Well done. I encourage other companies to innovate and adapt. pic.twitter.com/XDqGY4UYhZ

— Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 (@AbiyAhmedAli) April 12, 2020