Fana: At a Speed of Life!

በባህላዊ ፍርድ ቤት ከ32 ሺህ በላይ ጉዳዮች መስተናገዳቸውን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም በባህላዊ ፍርድ ቤት ከ32 ሺህ በላይ ጉዳዮች መስተናገዳቸውን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስታወቀ፡፡

ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምክክር የተካሄደ ሲሆን ፥ በመድረኩ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ያጋጠማቸው ተግዳሮቶች እና በጎ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።

ባህላዊ ፍርድ ቤት በጨፌ ኦሮሚያ አዋጅ ቁጥር 240/2013 ፀድቆ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በ2015 ዓ.ም ብቻ 32 ሺህ መዝገቦች ውሳኔ መስጠቱን የዞኑ አስተዳደር ሚስኪ መሀመድ ተናግረዋል።

32ሺህ በላይ ጉዳዮች ወዲያውኑ ውሳኔ ሲሰጣቸው ፥ የተቀሩት ደግሞ ለመደበኛ ፍርድ ቤት መተላለፋቸውን አስተዳዳሪዋ አንስተዋል።

ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ በዞኑ 296 ቀበሌዎችና 24 ከተማዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቶች በአቅም ረገድ ያጋጠማቸውን ተግዳሮት ለመፍታት ከሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር እንደሚሰራም ነው የተናሩት።

የባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ መኖር በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ መጨናነቆች መቀነሳቸውን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተወካይ ገልፀዋል።

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.