Fana: At a Speed of Life!

የክልሎች አፈ-ጉባኤዎች በጋምቤላ ክልል የሚገኘውን ባህላዊ የወርቅ አምራቾችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁሉም ክልል አፈ-ጉባኤዎች ፎረም በጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ የሚገኘውን የሉንጋ ቀበሌ ባህላዊ የወርቅ አምራቾችን እና የአልዌሮ ግድብን ጎበኙ።

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ በጉብኝቱ ወቅት÷ በክልሉ ለኢንቨስትመንት አማራጭ የሚሆን  መሬት፣ ውሃ፣ ማዕድንና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡

የሁሉም ክልሎች የአፈ-ጉባኤዎች ፎረም በጋምቤላ ክልል መካሄዱ ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ልማት ለማስገባት ያግዛልም ነው ያሉት፡፡

ፎረሙ አንዱ ክልል ከሌላው ክልል ልምድ በመውሰድ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያጠናክርም ጠቁመዋል፡፡

የክልሎች አፈ-ጉባኤዎች የጋምቤላ ክልል ለልማትና ለኢንቨስትመንት ምቹ ነው ማለታቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.