የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

March 15, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፥በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መክረዋል፡፡

የቆየውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በተጨማሪም በውይይት ኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስማማታቸውን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት ማግኘቱንም አመልክቷል።

በኢኮኖሚው፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም በውይይቱ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።