Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒ ብሊንከን የመጀመሪያውን የአሜሪካ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካን ግቢ የሚገኘውን የመጀመሪያውን የአሜሪካ ኤምባሲ ቆንስላ ጽሕፈት ቤትን ጎበኙ።

አሜሪካን ግቢ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ አንፀው ይኖሩበት እንደነበር ይታወቃል፡፡

በ1930 ዎቹ የአሜሪካ ኤምባሲ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ሆኖ ማገልገሉም ይታወሳል፡፡

በኋላም የየመን ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ሆኖ ማገልገሉን አስታውሶ ኢፕድ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ ከዓለም ቅርሶች ፈንድ ጋር በመተባበር በአሜሪካ ግቢ የሚገኘውን በፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የታነፀ ታሪካዊ ሕንፃ አድሶ ማስመረቁ ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.