የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
አስተዳደሩ የህዝቡን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚሰሩ የመጀመሪያ ዙር 100 ሺህ ቤቶችን ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
ለመጀመሪያ ዙር ግንባታም በመንግስት 350 ሺህ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው፡