በቻይና ከውጭ ሃገራት የገቡ 108 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ከውጭ ሃገራት የገቡ አዳዲስ 108 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ።
የሃገሪቱ የጤና ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ ከተለያዩ ሃገራት የገቡ ሰዎች ላይ በተደረገ ልየታና ክትትል 108 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ይህ ቁጥር ቻይና የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠሯን ከገለጸች በኋላ በሳምንት ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛው መሆኑም ነው የተነገረው።
በቻይና 83 ሺህ135 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 3 ሺህ 219ኙ ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።
77 ሺህ 956 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ