አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቆይታቸውን አጠናቀዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አሸኛኘት እንዳደረጉላቸው የዘገበው ኢዜአ ነው።
አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማምተዋል።
በውይይቱ በኢኮኖሚ፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይም በግብርና እና ቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም ትኩረት እንደተሰጠባቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን ጠቁመዋል።
አሜሪካ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እንዲጠናከር እያደረገች ያለውን ድጋፍ በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡
#Ethiopia #AbiyAhmedAli #Blinken #EthioAmerica #america
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!