Fana: At a Speed of Life!

የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት የኢትዮጵያና አሜሪካ ወዳጅነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመሸጋገሩ ማሳያ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7 2015 (ኤፍ ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወዳጅነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመሸጋገሩ ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷የሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሀገራቱን ትብብርና ወዳጅነት ወደ ተሻለ እና አዲስ ትብብር እየተሸጋገረ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

 

ሚኒስትሩ በቆይታቸው÷ በቀጠናዊና የሀገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል፡፡

 

በተጨማሪም አንቶኒ ቢሊንከን 331 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ ይፋ ማድረጋቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

 

የሰላም ሒደቱ ዘላቂ እንዲሆን የአሜሪካ መንግስት ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚፈልግ መግለጻቸውንም ጠቁመዋል፡፡

 

ከሰላም ማስከበር በተጨማሪ አሸባሪነት፣ የባህርላይ ውንብድና እንዲሁም ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሻከረን ግንኙነት የማለዘብ፣ የተዛባ እይታ ያላቸውን የማስገንዘብ እና ወዳጅን የማብዛት አካሄድ እየተከተለች መሆኑንም አምባሳደር መለስ ጠቁመዋል፡፡

በሐብታሙ  ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.