Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ ምላሽ ለመስጠት ከ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ያስፈልጋል – ተመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን የሰብዓዊ ምላሽ ለመስጠት ከ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታውቋል፡፡

ቢሮው በኢትዮጵያ ያለውን የድርቅ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት÷ ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች በቂ ዝናብ ባለመጣሉ  በደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ የሚባል ድርቅ መከሰቱን ገልጿል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የምግብ እጥረት መፈጠሩን እና በአሁኑ ወቅት 24 ሚሊየን ዜጎች ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በድርቁ ምክንያት 11 ሚሊየን ሰዎች ለምግብ ዋስትና ችግርተጋልጠዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን÷ እስካሁን 6 ነጥብ 85 ሚሊየን የሚጠጉ እንስሳትም መሞታቸው ተጠቁሟል፡፡

በሀገሪቱ ያለው ድርቅ እና ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች የዜጎችን የሰብዓዊ ፍላጎት ሊጨምር እንደሚችል በመጠቆም÷ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ኦቻ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ኦቻ በፈረንጆቹ 2023 በኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ሰብዓዊ ምላሽ ለመስጠት ከ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ለዚህም የተራድኦ ድርጅቶች በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል ፈጣን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ኦቻ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.