አንቶኒ ብሊንከን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ተወያይተዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
በህብረቱ ዋና ፅህፈት ቤት የተደረገው ውይይታቸው፥ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ግጭት እና ጦርነቱ እንዲቆም የተደረሰው የሁለቱ አካላት ስምምነት አፈፃፀምን ተመልክቷል።
በተጨማሪም በሌሎች የጋራ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን ነው ሊቀመንበሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ያመለከቱት።