የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በስብሰባው በተለያዩ ሀገራዊ፣ ፓርቲያዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር የኢትዮጵያን ብልፅግና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማረጋገጥ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሚመክር ይሆናል ነው የተባለው።
ስብሰባው በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡