Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የአባል ሀገራቱ ሚኒስትሮችን ጨምሮ  የአጋርና ባለድርሻ  አካላት ከፍተኛ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ በቀጠናው ያለውን  የክህሎት ልማትና የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣  የፍልስት ተመላሾች አስተዳደር፣ ከስደት ተመላሾችን ማቋቋሚያ እና ስርዓተ ጾታን በሚመለከት ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዳያስፖራና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በተመለከተ እንዲሁም በዙርፉ የቆንስላዎች አስፈላጊነት ዙሪያ የተዘጋጁ ሰነዶች ይጸድቃሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመጫረሻም ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ  እና ስምምነቶችን በመፈራረም ፎረሙ ይጠናቀቃል መባሉን ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.