Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ተግዳሮቶች የሀገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደጎዱት ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ችግሮችን ተከትሎ የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱ ተገለፀ።
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዘርፍ እየፈተኑ ባሉ ተግዳሮቶች ላይ መፍትሄ ለማምጣት ያለመ ውይይት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ይገኛል፡፡
በውይይቱ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ÷ ዘርፉ ትልቁን የሃገር የምጣኔ ሀብት አቅም የሚያንቀሳቅስ ቢሆንም እየገጠሙት ያሉት ችግሮች ግን ለሃገር ኢኮኖሚ የራሱን አስተዋጽኦ ለመወጣት እንዳይችል በብዙ ፈትነውታል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ሰብሳቢ ኢንጂነር ግርማ ሃብተ ማርያም፥ በተከታታይ እየተስተዋለ ያለው የግንባታ ግብአቶች ዋጋ ንረት ለዘርፉ ተግዳሮት ከሆኑ ችግሮች ቀዳሚው እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ችግሮቹንም በዘላቂነት ለመፍታት በመንግስት በኩል አስፈላጊው መፍትሄ ሊወሰድ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
በተለይም ከግዥና ሌሎች የአሰራር ሂደቱን በተመለከተ የዘርፉን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን በመተግበር፣ መንግስትንና ተቋራጩን የሚያቀራርብ ስራ ሊኖር እንደሚገባም አንስተዋል።
በሌላ በኩል የውጭ ሀገር ተቋራጮች ጋር የሚደረገው የጨረታ ሂደትን በተመለከተም የሀገር ውስጥ ተቋራጩን ያገናዘበ ሊሆን ይገባል የሚል ሃሳብንም አንስተዋል።
በይስማው አደራው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.