ስፓርት

ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን አሰናበተ

By Mikias Ayele

March 17, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራን ማሰናበቱን አስታወቀ።

ክለቡ ፈረንሳዊውን የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ ከአሰልጣኝነት እንዳሰናበተው ቢቢሲ አስነብቧል።

የደቡብ ለንደኑ ክለብ ባለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

በፕሪሚየር ሊጉም ከ27 ጨዋታዎች 27 ነጥብ በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።