በኮንሶ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ የ13 ሰዎች ሕይወትአለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ገርጨ እና አይሎታ ደካቱ ቀበሌዎች ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት 13 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወሰዱ፡፡
ዞኑ እንዳስታወቀው÷ የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በሰገን ዙሪያ ወረዳ ዶዴ እና መገርሳ ወንዞች ነው፡፡
በአካባቢው አሁን እየዘነበ ያለው ዝናብ ከአራት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዝናቡን ተከትሎም ህብረተሰቡ ለተጨማሪ የጎርፍ አደጋ እንዳይጋለጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል፡፡
በተጨማሪም በህፃናትና ታዳጊዎች በወንዞች አቅራቢያ እንዳይንቀሳቀሱቨህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አስተዳደሩ ማሳሰቡን ከኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡