Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በ82 ሚሊየን ብር የመልሶ ማቋቋም ሥራ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ግጭት ተከስቶ ከነበረባቸው ሁለት ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 82 ሚሊየን ብር መድቦ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

በዚህም ከደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ፣ ደራሼና አሌ ልዩ ወረዳዎችን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ የሚገኙ አምሥት ወረዳዎች የመልሶ-ማቋቋም ሥራው ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለአንድ ዓመት በቆየው የፕሮጀክቱ በጀት ተፈናቀሉ ወገኖች የቤት ግንባታ፣ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ ድጋፍ ፣ የውሃ አቅርቦት እና የቁሶች ጥገና እንዲሁም የሥነ ልቦና ድጋፎች ሲተገበሩ መቆየታቸውም ተመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ቅድሚያ የሠጠ መሆኑ ተነግሯል፡፡

830 ሰዎች በቤት ግንባታ ተጠቃሚ ሲሆኑ የ760 ሰዎችን ኑሮ መደገፍ ያስቻለ መሆኑም ተነስቷል፡፡

ፕሮጀክቱን በጥራት ማከናወን እንዲቻል 174 በጎ ፈቃደኞችን በማሰልጠን፣ 24ቱን በቋሚነት፣ 150ውን በየአካባቢያቸው ተሰማርተው ሥራውን በቅርበት እየተከታተሉ ተጠቃሚዎችን እንዲያግዙ በማድረግ ላለፈው አንድ ዓመት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷልም ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ቀደም ሲልም በ24 ሚሊየን ብር 280 ቤቶችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.