Fana: At a Speed of Life!

በ60 ሚሊየን ብር ወጪ መልሶ የተገነባው የመጠጥ ውሃ ተቋም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ብሔራዊ ክልል ጨርጨር ወረዳ በጦርነቱ ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበረው የውሃ ተቋም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በምረቃ መርሐ-ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ÷ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የፌደራል መንግስት በጦርነት የተጎዱ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በተለያየ መንገድ እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርም የንጹህ መጠጥ ወሃ አቅርቦት ላይ የመልሶ ግንባታ እያከናወነ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የውሃ መሠረተ ልማቱ የዲዝል ፓምፕ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በሶላር ፓምፕ በመቀየር አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን በመጥቀስ ከዲዝል ፓምፕ ወደ ሶላር ፓምፕ መቀየሩ የነዳጅ ከፍተኛ ወጪን እንደሚያስቀርም ነው ያነሱት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የሚኒስቴሩ ባለሙያዎች ከፌደራል መንግስት ተወካይ አስተባባሪዎች፣ ከወረዳው አስተባባሪዎችና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በአስቸጋሪ ሁኔታ ሶስት ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.