የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “የመደመር ትውልድ” መፅሐፍ ላይ ምልከታቸውን ያቀረቡ ምሁራንን አመሰገኑ

By Alemayehu Geremew

March 18, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የመደመር ትውልድ” መፅሐፍ ላይ ምልከታቸውን ያቀረቡ ምሁራንን አመሰገኑ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በምረቃው ሥነ-ስርዓት ላይ ከ500 በላይ ወጣቶች እንዲገኙ ማድረጋችን የመደመርን ትውልድ ለመገንባት የጀመርነው ሥራ አካል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የ“የመደመር ትውልድ”ን ሁሉም እንዲያነበው፤ እንዲወያይበት እና እንዲተቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋብዘዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈው “የመደመር ትውልድ” መፅሐፍ ዛሬ በታላቁ ቤተ መንግስት ተመርቋል፡፡

መፅሐፉ በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ነው፡፡