የሀገር ውስጥ ዜና

እስከ ፊታችን ማክሰኞ የሚቀጥል ነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው

By Meseret Awoke

March 19, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ30ሺህ ኢትዮጵያውያን እስከ ፊታችን ማክሰኞ የሚቀጥል ነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡

በአለርት ሆስፒታል የነጻ ህክምና አገልግሎቱ መክፈቻ ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን ፥ አገልግሎቱ በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልና በአዲስ አበባ አለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየተሰጠ ይገኛል።

ነጻ የህክምና አገልግሎቱ የሳውዲ በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው አልባሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ከያሲን ፈውንዴሽን ጋር በመተባበር እየሰጡ ነው፡፡

ይህም አገልግሎት ከየካቲት 23 እስከ መጋቢት 12/2015 ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም 30ሺህ ዜጎች የነጻ የዓይን ህክምናተጠቃሚ እንደሚሆኑ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ ዶ/ር ዳንኤል ገ/ሚካኤል እንዳሉት ፥ አልባሳርና ያሲን ፋውንዴሽን ለ 23 ዓመታት ከ 500 ሺህ በላይ የዓይን ህክምና አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

የሳውዲ አረቢያና የፓኪስታን አምባሳደሮች እንዲሁም አልባሳርና ያሲን ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጆች ከጤና ሚኒስቴር ጋር አብረው በዓይን ህክምናና በሌሎች የጤና አገልግሎቶች ላይ ተባብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

#Ethiopia #eyes #health

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!