የሀገር ውስጥ ዜና

የገቢ ንቅናቄ ማስጀመሪያና የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Shambel Mihret

March 19, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ሀሳብ የገቢ ንቅናቄ ማስጀመሪያና የግብር ከፋዮች እውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በ2014 የግብር ዘመን የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ በታማኝነትና በወቅቱ ለተወጡ 300 ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በየሻምበል ምህረት