የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ጤና ድርጅት 35 ሜትሪክ ቶን የድንገተኛ አደጋ የሕክምና ቁሳቁስ ለትግራይ ክልል እያከፋፈለ ነው

By Alemayehu Geremew

March 20, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ የሕክምና መሥጫ ቁሳቁስ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማት እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ አቅርቦቱን የላከው ከአውሮፓ ኅብረት ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ዕርዳታ፣ ከአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት እንዲሁም ከተመድ የድንገተኛ አደጋ ፈንድ ጋር በመተባበር ነው፡፡

35 ሜትሪክ ቶን የሕክምና መሥጫ ቁሳቁሱ በትግራይ ክልል እየተከፋፈለ መሆኑንም ከገጹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አቅርቦቱ በክልሉ የሕክምና ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 700 ሺህ ያኅል ሰዎች የሚውል ሲሆን፥ በክልሉ ማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች ለሚገኙ 48 የጤና ተቋማት እየተከፋፈለ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡