ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ እና ቻይና “መልካም ጎረቤታሞች” እና “የሚተማመኑ አጋሮች” ናቸው – ሺ ጂንፒንግ

By Alemayehu Geremew

March 20, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ቻይና “መልካም ጎረቤታሞች” እና “የሚተማመኑ አጋሮች” ናቸው ሲሉ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

ሺ ጂንፒንግ የሩሲያ ጉብኝታቸውን በጀመሩበት ወቅት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ ደርሰዋል።

ሺ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ባደረጉት ንግግርም ከጦርነቱ በኋላ ወደ ሩሲያ ያደረጉት የመጀመሪያው ጉብኝት እንደሆነ አንስተዋል።

ጉብኝቱም ለሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት “አዲስ መነቃቃት” ይፈጥራል ብለዋል።

ለቀጣይ የቻይና እና የሩሲያ ጤናማ እና የተረጋጋ ግንኙነት መዳበር የሥራ ጉብኝታቸው ፍሬያማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።