Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የሰላም እና ባህል ማበልፀጊያ ተቋም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የሰላም እና ባህል ማበልፀጊያ ተቋም በይፋ ተመረቀ፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ግብዣ የተደረገላቸው እግዶች ተገኝተዋል፡፡

ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ሕዝቦች የረዥም ጊዜ ታሪካዊ ወዳጅነትን አስታውሰዋል፡፡

የመሰል ተቋማት መገንባት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን የበለጠ ያጠናክሩታል ማለታቸውን በጅቡቲ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.