Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡
በዚህም መሰረት አቶ መምህሩ ሞኬ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ ከበደ ጋኖሌ የክልሉ የዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አድርጎ ሹሟል።
እንዲሁም አቶ መኩሪያ ማርሻሄ የክልሉ የከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ አሰፋ ጉራቻ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ እና ዶክተር ዳዊት ሐዬሶ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት የክልሉን የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥ የሰላሳ ዳኞችን ሹመት አፅድቋል።
የተሾሙት ዳኞች በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ወረዳ ፍርድ ቤቶች አንደሚሰሩ ነዉ ዳኞችን ለሹመት ያቀረቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱለቻ የተናገሩት።
ከዚህም ባሻገር የክልሉ ምክር ቤት የቀረቡለትን ሦስት አዋጆች መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት የክልሉን የመሬት አጠቃቀም አዋጅ፣ የክልሉን የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር አዋጅ እና የክልሉን የማረሚያ ተቋማት አስተዳደር አዋጅ መርምሮ ተግባራዊ እንዲያደርጉ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
በቢቂላ ቱፋና ታመነ አረጋ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.