የሀገር ውስጥ ዜና

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለጸ

By Meseret Awoke

March 21, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች ቡድን በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ካውንስለሮቹ ከአጎዋ ተጠቃሚነት ዕድል መቋረጥ ጋር ተያይዞ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በፓርኩ ከሚሠሩ ባለሀብቶች ጋር መክረዋል፡፡

በፓርኩ ከ22 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ኢንቨስት በማድረግ ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል ።

#Ethiopia #industrialparksdevelopmentcorporation #america #AGOA ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!