Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በ2030 የቲቢ በሽታን ለማጥፋት ቁርጠኛ ነው- ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በ2030 የቲቢ በሽታን ለማጥፋት ቁርጠኛ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቲቢ በሽታን ለመከላከል የተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

17ኛው የቲቢ የምርምር ጉባኤ “የቲቢ በሽታን ለማጥፋት ሀገር በቀል መፍትሄ” በሚል መሪ ሀሳብ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የቲቢ ምርምር አማካሪ ምክር ቤት ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በምክር ቤቱ የቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

ባለፉት ሀሉት አስርት ዓመታት የዘርፉ ምሁራን የቲቢ በሽታን ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከናወናቸውንም ነው የተናገሩት።

በቀጣይም የቲቢ በሽታን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ምክር ቤቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ ይቀጥላል ነው ያሉት።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የቲቢ ምርምር ምክር ቤት ቁልፍ ሚና መጫወቱን አንስተዋል።

የቲቢ በሽታ አሁንም የሰው ልጅ ስጋት ነው ያሉት ዶክተር ሊያ እንደ ሀገር በሽታውን ለማጥፋት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.