Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 109 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መለሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር 109 ፍልሰተኞች በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ከፍልሰተኞቹ መካከል 92ቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ደላሎች ምድረበዳ ላይ ተሰውረውባቸው በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት መጠለያ ጣቢያ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

17ቹ ደግሞ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ፍልሰተኞቹ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመካከኛው ምስራቅ ሀገራት በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚል ምኞት ተታልለውና ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ከሀገራቸው መውጣታቸው ተመላክቷል፡፡

ፍልሰተኞቹ በመሸጋገሪያና መዳረሻ ሀገራት ለረሃብ፣ ለውሃ ጥም፣ ለጤና መታወክ፣ ለከፍተኛ እንግልትና ተያያዥ ችግሮች መዳረጋቸውን ከኤንባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ኤምባሲው የኢትዮጵያ ወጣቶች በህገ-ወጥ ደላሎች የውሸት ስብከት በመታለል ውድ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.