የሀገር ውስጥ ዜና

“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

March 21, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ እና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ባለሃብቶች፣ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሦስት ቋንቋዎች የተጻፈው እና በቅርቡ የተመረቀው “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ ከመደመር ሐሳብ ጋር በተያያዘ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈ ሦስተኛው መጽሐፍ ነው።

በገመቺስ ታሪኩ