Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ኢትዮጵያን ጨምሮ በድርቅ ለተጎዱ ሀገራት የሚውል የ25 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ ፣ኬንያ እና ሱዳን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን በዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኩል የተበረከተ ሲሆን ፋኦ ድጋፉን ከጀርመን መንግስት መረከቡን አስታውቋል፡፡

ፋኦ ሪፖርቱ እንደገለፀው በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ የምግብ ዋስትና እጦትን እያስከተለ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን 22 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በድርቁ ምክንያት በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸውን እና በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አመላክቷል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ እና መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል የተባለ ሲሆን አንድ ሚሊየን ዜጎችን ለመርዳት ያስችላል ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.