Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን የግል ባለኃብቱ ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን የግል ባለኃብቱ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።

በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ከ350 በላይ ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ አቶ መላኩ አለበል፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አቶ ዓለሙ ስሜ፣ ባለኃብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኤክስፖው ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተመረቱ ምርቶች፣የተገኙ ውጤቶችን በሀገር፣ አህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው ተብሏል፡፡

የአምራቾችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከር፣ ልምድ እንዲለዋወጡ ማስቻል እና የገበያ ዕድሎችን መፍጠርም የኤክስፖው አላማ መሆኑ ታውቋል።

በኤክስፖው ላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ በአምራች ዘርፉ የሚሳተፉ 350 ድርጅቶች ምርቶታቸውን ይዘው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

300 ሺህ የሚጠጉ ጎብኚዎች በኤክስፖው ላይ እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን÷ የፌደራልና የክልል መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣የንግድ ማኀበራት፣ ላኪዎች እና ባለኃብቶች እንደሚሳተፉ ኢዜአ ዘግቧል።

አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ንቅናቄው በቀጣይነት ይበልጥ እንዲጠናከር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.