የሀገር ውስጥ ዜና

ሳንቫዶ የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ 120 ቶን የአቮካዶ ዘይት ለውጭ ገበያ አቀረበ

By Tamrat Bishaw

March 22, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳንቫዶ የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ 120 ቶን የአቮካዶ ዘይት ለውጭ ገበያ ማቅረቡ ተገለጸ፡፡

በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገኙ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳንቫዶ የአቮካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ በ2015 በጀት ዓመት ለሶስት ዙር 120 ቶን ኦርጋኒክ ዘይት ለውጭ ገበያ ማቅረቡ ተገልጿል፡፡

ፋብሪካው ሆላንድ የምርቱ ዋና መዳረሻ ገበያ እንደሆነችም ተገልጿል፡፡

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድም ከ80 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ጋር የምርት ትስስር እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ከ120 በላይ ለሆኑ ዜጎችም ቋሚ እንዲሁም ከ200 በላይ ለሚሆኑት ጊዜያዊ የስራ እድል እንደፈጠረ መገለጹን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡