ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከቻይናው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሥራ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በቻይናው የአውሮፕላን አምራች ዳይመንድ ኤርክራፍት ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሊኩዊን ዣንግ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
ኮሚሽነር ለሊሴ በውይይቱ ላይ÷ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ ማበረታቻዎች እና በዘርፉ የተተገበሩ የሕግ እና የፖሊሲ ማሻሻያዎችን አብራርተዋል፡፡
መንግስትም ዘርፉን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ኩባንያው በኢትዮጵያ በአቪየሽን አምራች ዘርፍ ለመሳተፋ ፍላጐት እንዳለው መገለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዳይመንድ ኤርክራፍት በቻይና የሚገኝ ግንባር ቀደም አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ነው፡፡