Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቤኔሉክስ ሀገራት የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቤልጂዬም፣ ኔዘርላንድስና ሉክዘምበርግ የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሮቹ የኢትዮጵያ መንግስት ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን ለመፍጠር እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን እና የሽግግር ፍትሕ ይፋ መደረጉም የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይ ሀገራቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት አጠናክረው ለማስቀጠል ቁርጠኛ እንደሆኑ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.