የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሚገነባው የመኖሪያ ህንፃ እና የእናቶች እንጀራ መጋገሪያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

By Shambel Mihret

March 23, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሚገነባው የመኖሪያ ሕንፃ እና የእናቶች እንጀራ መጋገሪያን ያካተተ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በእንጦጦ አካባቢ ለሚገነባው ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ማዕከሉ ባለ 10 ወለል ህንጻ ሲሆን በውስጡ 100 የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የያዘ ሲሆን÷ የግንባታው ወጪ ሙሉ ለሙሉ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በስድስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለነዋሪዎች እንደሚተላለፍም ተጠቁሟል፡፡

በማህሌት ተክለብርሃን