Fana: At a Speed of Life!

ከውጭ የሚገባውን የእንስሳት አልሚ ምግብ በሀገር ውስጥ እያመረተ ያለው ግለሰብ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለማየሁ አሣዬ “እንደ ሰው ልጆች ሁሉ እንስሳትም አልሚ ምግብ ያስፈልጋቸዋል” በሚል ዕሳቤ ለእንስሳት አልሚ መኖ እያመረተ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ እንስሳት ጤና እና ምርታማነት እንዲጠበቅ የበኩሌን አስተዋጽዖ እያደረግኩ ነው ይላል፡፡

የፈጠራ ባለሙያው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበረው ቆይታ፥ ለእንስሳት መኖ ማበልፀጊያነት የሚያገለግለውን አልሚ መኖ የማምረት ሥራ በ2007 ዓ.ም መጀመሩን ተናግሯል፡፡

ለዚህ ሥራውም የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የባለቤትነት ፈቃድ እንደሰጠው ይናገራል።

አስገዳጅ ደረጃዎች ያሟላ እና ጤናማ ምርት ስለመሆኑም ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይሁንታን አግኝቷል ነው ያለው፡፡

ምርቱ ከኬሚካል የፀዳ እና ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) በመሆኑ፥ ለእንሳስት ጤና፣ ዕድሜ እና ጉልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጿል፡፡

ምርቱ ከውጭ ሀገር ቢገባ ለአንድ ኪሎ ግራም እስከ 250 ብር ወጪ እንደሚጠይቅ እና በሀገር ውስጥ እየተመረተ ያለው ግን በ90 ብር መሆኑንም ነው የተናገረው።

በዱቄት፣ እንክብል እና አሞሌ መልክ÷ በ1፣ 2 እና 35 ኪሎ ግራም እንደሚዘጋጅም አብራርቷል፡፡

ምርቱ ለእንስሳት አርቢዎች፣ አድላቢዎች እንዲሁም ለእንስሳት መድኃኒት ቤቶች እንደሚጠቅምም አንስቷል፡፡

ከየትኛውም የእንስሳት መኖ ጋር በሚፈቀደው መጠን ልክ ቀላቅሎ መስጠት እንደሚቻል ይመክራል፡፡

ይህ የፈጠራ ውጤት የእንስሳት ተዋጽኦን መጠን፣ ከእንስሳት የሚገኝን አገልግሎት ብሎም ገቢ እንደሚያሳድግ ነው ያስረዳው፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.