Fana: At a Speed of Life!

የዓየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋም በየዓመቱ 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በየዓመቱ 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የብሪታኒያ የኃይል ሽግግር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት የዓለም ኢኮኖሚ ከካርበን ልቀት ነፃ መሆን የሚችልበትን አማራጮች ማመላከቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የተገለጸው የገንዘብ መጠን እጅግ ብዙ ቢሆንም ከብክለት የፀዳች ዓለም ከተፈለገ ግን ግዴታ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ያመላከተው።

የኮሚሽኑ ሪፖርት ገንዘቡ ከፈረንጆቹ 2030 ጀምሮ እስከ 2050 ድረስ የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቅሷል።

ይህም አሁን ላይ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከሚወጣው 1 ትሪሊየን ዶላር በእጥፍ የሚልቅ ይሆናል።

ይህ ገንዘብ እስከ ፈረንጆቹ 2050 ሥራ ላይ የሚውል ከሆነ የተፈለገውን ራዕይ ማሳካት እና በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ቀውስ መግታት እንደሚቻልም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ የኃይል አማራጮች ላይ የሚመክሩ መሪዎች ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው።

ሀገራትም የባሰው መጥፎ ጊዜ ከመምጣቱ አስቀድመው የታዳሽ ኃይልን መጠቀም እንደሚገባቸውም ሪፖርቱ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

ጥምረቱ የፓሪሱን ሥምምነት ዓላማ ከጉዳይ በማስገባት በተጣጣመ መልኩ ይሠራልም ነው የተባለው፡፡

በፈረንጆቹ 2015 የዓየር ንብረት ለውጥ ላይ በፓሪስ የመከረው ጉባዔ የዓለም ሙቀት መጨመርን ከ2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በታች ለማውረድ እና 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ላይ ለመገደብ ሥምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.