ከተሞች ለነዋሪዎች እንዲመቹ እየተሠራ መሆኑ ተመለከተ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ።
በአዲሱ የቤት ልማት ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ውይይት በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።
በሚኒስቴሩ የከተማ ቤቶች አቅርቦትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ፀጋዬ ሙሼ እንደገለፁት፥ በከተሞች የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ እየተሠራ ነው።
የቤት ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ፣ ያረጁና ከደረጃ በታች የሆኑ ቤቶች መብዛት እንደችግር ተነስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች ለቤት ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ ጠቁመው÷ ከተሞች ለመኖሪያ ቤት መስፋፋት ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም ጤናው፥ የከተሞችን ትስስር ለማጠናከርና ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የልምድ ልውውጥና የትብብር መድረክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ከሀገሪቱ ከ80 በላይ ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎችና ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
በሰላም አሰፋ