Fana: At a Speed of Life!

የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆኗል።

የዳሰሳ ጥናቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አቡ ካምፖ፣ ሚኒስትሮችን ጨምሮ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ነው በአዲስ አበባ ይፋ የተደረገው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንየተመጣጠነ ምግብ መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ግጭትን በማስቆም፣የኑሮ ውድነትን በመቀነስ እና ምርታማነትን በማሳደግ የተመጣጠነ ምግ ችግሩን መቅረፍ ይገባል ብለዋል።

የተመጣጠነ ምግብ እና የስርዓተ ምግብ ጉዳይ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን በመጥቀስም፥ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ከስርአተ ምግብ ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

የስርዓተ ምግብ ችግር አሁንም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አቡ ካምፖ የኢትዮጵያ መንግስት የዳሰሳ ጥናቱን ለማውጣት ላደረገው ጥረትና ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የህጻናትን አቅም እንደሚያጠፋ ያነሱት ተወካዩ፥ ችግሩን ለመፍታትና አካባቢያዊ መፍትሄ ለማግኘት ከማህበረሰቡ ጋር በቅርበት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው የዳሰሳ ጥናት በኢትዮጵያ በተለይም በህጻናት ላይ የሚከሰተውን የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ለማስወገድ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.