Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ እና ኢትዮጵያ አዲስ የንግድ አጋርነት መመሥረት የሚያስችላቸውን ጉባዔ እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል የምጣኔ ሐብት፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብሮች ያጠናክራል የተባለለት የቢዝነስ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ከተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተውጣጡት የቱርክ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ አካላት ጋር በጉባዔው ላይ ተገናኝተዋል፡፡

ልዑካኑ ከምግብ ማቀነባበሪያ ፣ ከጨርቃጨርቅ ፣ ከኅንፃ ግንባታ ቁሳቁስ እና ማሽን አምራች ድርጅቶች እና ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎን የቱርክ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻ የንግድ አጋሮቻቸው ጋር የተለያዩ ሽርኮችን ለመፈጸም ይወያያሉም ተብሏል፡፡

በንግዱ ዘርፍ የሚሳተፉት የቱርክ ባለሐብቶች ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ያስቻለው ጉባዔ ዕውን የሆነው የቱርኩ የጥቁር ባሕር ላኪዎች ማኅበር ልዑካን ቡድን ከሀገሪቷ ንግድ ሚኒስቴር እና ላኪዎች ጉባዔ ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ ነው፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ መረጃ እንዳመላከተው በሀገራቱ መካከል አዲስ የንግድ አጋርነቶችን ለመመሥረት የዛሬው ሁነት አዲስ መሠረት የሚጥል ይሆናል፡፡

በወንደሰን አረጋኸኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.