የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በጉሙሩክ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

March 23, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በጉሙሩክ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የሀገራቱን ጉምሩክ አገልግሎት አሰጣጥ የተቀላጠፈና የዘመነ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

ባለሥልጣናቱ ለ3 ቀናት በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ከተለዋወጡ በኋላ ስምምነትላይ መድረሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ዓለም አቀፋዊ መሥፈርቶችን ማዕከል ያደረገ እና ውጤታማ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ዕውን ማድረግ ለነገ የማይባል መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል የተባለውን የጋላሞ-ሞሎድ መንገድን ግንባታ ለማጠናቀቅ ስምምነት መደረሱ ተገልጿል፡፡

35 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋላሞ- ሞሎድ መንገድ÷የሀገራቱን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳደግ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡