Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶች ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ ይገባል – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ም/ሃላፊ ተፈሪ ታረቀኝ እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ በስራ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ ዩኒሰን የምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ፣ ራቫል የብረታ ብረት ማምረቻ፣ ገደፋው ብረታ ብረት (አይ ቬ ኮ) የመኪና ጥገናና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ መላኩ አለበል÷ የባሕር ዳር ከተማ ለዘርፉ የሰጠውን ልዩና አበረታች ትኩረት አድንቀዋል፡፡

በክልሉ ሌሎች ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶችም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በበቂ ሁኔታ ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለውንና በቅርቡ መገጣጠሙ የተጠናቀቀለትን ዘመናዊ የዓባይ ድልድይ የደረሰበትን ደረጃም መጎብኘታቸውን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.