Fana: At a Speed of Life!

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል፡፡

የ38 ዓመቱ አጥቂ ትናንት ምሽት ሀገሩ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በመሰልፍ ሁለት ጎሎችን በቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው መሰለፉን ተከትሎ ሮናልዶ ለሀገሩ 197 ጨዋታዎችን በማድረግ ለብሔራዊ ቡድን በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ በኩዌቱ አጥቂ ባድር አል ሙታዋ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽሏል፡፡

በተጨማሪም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ2004 ጀምሮ ለ20 ተከታታይ አመታት ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ማስቆጠር የቻለ ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት 120 ማድረስ ችሏል፡፡

በትናንትናው ጨዋታም 60ኛ የቅጣት ምት ጎሉን በስሙ አስመዝግቧል፡፡

ለሳዑዲው አልናስር የሚጫወተው ሮናልዶ በቀድመው የፖርቹጋል አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ የቋሚ አሰላለፍ እድል ተነፍጎት የነበረ ሲሆን በአዲሱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ደግሞ የቡድኑ አምበል እና ቋሚ ተሰላፊ መሆን ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.