Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ በኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ሀገራት ቋሚ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰመሪታ ሰውሰው በኢትዮጵያ የአረብ መንግስታት ሊግ ቋሚ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮን ኃላፊ ከሆኑት ዶክተር ዋሊድ ሀመድ ሺልታህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የአለም አቀፍ የሰብአዊ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ህብረት እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ቋሚ ተወካይ ኢቶነዴ ካኮማም ተገኝተዋል፡፡

ምክክሩ በኢትዮጵያ እና በአረብ ሀገራት ሊግ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ የረጅም ጊዜ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ትስስሮችን በማሳደግ የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንትና የልማት እድሎችን በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ቀንድ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በምግብ ዋስትና ዙሪያ በፀደቀው ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ላይ ያተኮረ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ግብዓቶችን የማሰባሰብ እድሎች ላይ ተወያይተዋል።

ሁለቱ አካላት በመጪው ዓመት ህዳር ወር መጨረሻ በሳዑዲ አረቢያ በሚካሄደው የአፍሪካ የአረብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የኢኮኖሚ ልማት፣ አካባቢ እና ባህልን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በሚኖረው ንቁ ተሳትፎ ፣ በመሪዎቹ ጉባኤ በሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይም መክረዋል።

እነዚህ መድረኮች ለአረብ ሀገራት ሊሆኑ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመለዋወጥ፣ የግብርና ምርታማነትን እና የአካባቢ ጥበቃን ለማሳደግ፣ ውጤታማ ፕሮግራሞችን ለማስተዋወቅ እና የባህል ትስስርን ለማጠናከር እንደ ዕድል ሊያገለግሉ ይችላሉ መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁለንተናዊ እና የተሟላ አቀራረብን ለማረጋገጥ በሚኒስቴሩ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ከአረብ አምባሳደሮች ምክር ቤት ጋር መደበኛ ውይይት ማድረግም ከተወያዩባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ይጠቀሳሉ።

#Ethiopia #ethiopianfinanceminister

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.