Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ የውሃ አጠቃቀም ስርዓትን ለማሻሻል በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ የውሃ አጠቃቀም ስርዓትን ለማሻሻል በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ በኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዓለም አቀፍ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ኪቲ ቫን ደር ሄይጅደን እና ከኔዳምኮ አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማይክል ኮግለር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ ኔዳምኮ አፍሪካ የተሰኘው ተቋም የሚያከናውነውን የተሻሻለ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት ማዕቀፍን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል፡፡

ማዕቀፉ ሜትሮፖሊታን ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ያለውን የውሃ አጠቃቀም ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ስርዓቱ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ እና የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የውሃ አጠቃቀም መጠንን መለካትና እና የሚከሰቱ ችግሮችን ለመለየት እንደሚረዳ ነው የተገለጸው።

በዚህ ማዕቀፍ ከ10 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ አስተዳደር ስርአት ነው የሚተገበረው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.